በኢትዮጵያ በማይከፈልባቸው የቤት ውስጥ ስራ ኃላፊነቶች ላይ ማህበራዊ ደንቦች እንዴት ተጽእኖ ያሳድራሉ?

በሂዳያ ሙሂደን እና ዶ/ር ክሪስቲ ድሩክዛ

ማህበራዊ ደንቦች ምንድን ናቸው?

ማህበራዊ ደንቦች የሰዎች ባህሪን ሊወስኑ ፣ መደበኛ ያልሆኑ እና ያልተጻፉ ሊሆኑ የሚችሉ ደንቦች ናቸው ነገር ግን ወደ ህጎች እና ፖሊሲዎችም ሊካተቱ ይችላሉ። በቢቺሪ እ.ኤ.አ 2017 መሰረት፣ ሰዎች ባህሪያቸው የሚወሰነው አካባቢያቸው ያሉ ሰዎች እንደዚህ አይነት ባህሪ ይኖራቸዋል ብለው ስለሚጠብቁ ነው፣ ወይም እንደዚህ አይነት ባህሪ ካላሳዩ ማዕቀብ ሊደርስባቸው ሲለሚችል ነው (ሐሜትና ስድብ ጨምሮ)። ይህ ትክክለኛ ባህሪ መሆኑን በውስጣቸው ሊያምኑም ላያምኑም ይችላሉ። ቢቺሪ ከተጨባጭ የሚጠበቁ ነገሮች እና መደበኛ ተስፋዎች መካከል ይለያያል። ተጨባጭ የሚጠበቁ ነገሮች ሌሎች ሰዎች ስለሚያደርጉት ነገር እምነት ሲሆን ፣መደበኛ ተስፋዎች ደግሞ ሌሎች ሰዎች እኛ ማድረግ ያለብን ነገር ብለው የሚያምኑት እምነት ነው። ማህበራዊ ደንቦች ለመለካት እና ለመለወጥ አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ።

የሥርዓተ-ፆታ ደንቦች ከልጅነት ጀምሮ በጣም ሥር የሰደዱ ናቸው። ይህም በሴቶች እና ወንዶች ልጆች መካከል በማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራ ኃላፊነቶች በመመደብ ላይ ከፍተኛ ልዩነት ያመጣል። ይህ ልዩነት በልጃገረዶች ደህንነት ላይ ከፍተኛ መዘዝ አለው፣ ምክንያቱም ለመማር፣ ለግል እድገት እና ለመዝናኛ ጊዜያቸውን ስለሚገድብ። እንደዚህ አይነት ደንቦች ወንዶች ለሴቶች ጊዜ ያላቸውን  ዋጋ ግንዛቤ ሊቀርጽ ይችላል፣ ይህም ልጃገረዶች እያደጉ ሲሄዱ የተወሰነ ሚና እንዲኖራቸው በማድረግ፣  እንደ አባት እና ተንከባካቢ የተገደቡ  ባህላዊ የፆታ ሚናዎችን ያጠናክራል።

በብዙ ማህበረሰቦች ውስጥ, ሴቶች ዝቅተኛ ማህበራዊ ደረጃ ሲሰጣቸው ወንዶች ብቸኛ ውሳኔ ሰጪዎች ናቸው። በዚህም ምክንያት ሴቶች ያልተመጣጠነ የማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራ ኃላፊነቶች እንደ ምግብ ማብሰል፣ ውሃ መቅዳት፣ ቡና ማፍላት፣ ልጆችን መንከባከብ እና ልብስ ማጠብ ይሰጣቸዋል፣ ይህ ደግሞ ለእረፍትም ሆነ ለራስ እንክብካቤ ጊዜ እንዳይኖራቸው ያደርጋል። በውጤቱም፣ የሴቶች እንቅስቃሴ በመገደቡ፣  የኑሮ ደረጃቸውን ለማሻሻልና ወሳኝ መረጃ የማግኘት እድልን ያሳጣቸዋል። በከተሞች ውስጥ እንኳን ሥራ ላይ ያሉ እናቶች  በማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራ ኃላፊነቶች ምክንያት የሥራ ጉዞ እና የሥልጠና እድሎችን በማጣት በሥራ ቦታ ምርታማነታቸው ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ።

የሥርዓተ-ፆታ ደንቦች ዘላቂነት በትውልድ ትውልዶች ውስጥ ይቀጥላል, ሴቶች ከወንዶች ጋር ሲነፃፀሩ እንደዚህ ባሉ ተግባራት ላይ ብዙ ጊዜ ማሳለፋቸውን ቀጥለዋል። ይህ እኩል ያልሆነ የማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራ ኃላፊነቶች ክፍፍል የሴቶችን የግል እድገት እና ጤና ከማደናቀፍ ባለፈ በህብረተሰቡ ውስጥ የፆታ እኩልነትን አለመኖርን ያስቀጥላል።

ኢትዮጵያ

ማህበራዊ ተቋማት በህብረተሰብ ውስጥ ተቀባይነት ያላቸው ወይም ተቀባይነት የሌላቸው የሚባሉትን ባህሪያት በመግለጽ የስርዓተ-ፆታ ሚናዎችን ይወስናሉ። የቡድኖች፣ ማህበረሰቦች እና ግለሰቦች ባህሪ በማህበራዊ ተቋማት እንደ መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ ህጎች፣ ማህበራዊ ደንቦች እና ልምዶች የተቀረፀ ወይም የተገደበ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶች የአዋቂዎች የማንበብ እና የመጻፍ ደረጃ ከወንዶች ያነሰ ነው። በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለው የአዋቂዎች የማንበብ ልዩነት 14.8 (ለወንዶች 59.2% እና ለሴቶች 44.4%) ነው። ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ የሚያሳደረው ተፅዕኖ ትልቅ እና ትውልድ ከትውልድ የሚተላለፍ ነው።

ብዙ ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የሴቶች ዝቅተኛ ማህበራዊ ደረጃ የሴቶችን የትምህርት እድል እና ማንበብና መጻፍ ችሎታ እንደ ምክኒያት ቢያቀርቡም፣ እውነታው ግን ሴቶች ስራ ይሰራሉ። እ.ኤ.አ. በ 2022 በኢትዮጵያ የሠራተኛ ኃይል ተሳትፎ መጠን ለወንዶች 86.2% እና ለሴቶች 75.0% ነው። በሥራ ላይ ያለው የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ቢሆንም፣ ሥራ ላይ ያሉ እናቶች የተለያዩ የሕፃናት እንክብካቤ ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል፣ ይህም በሥራ አፈጻጸማቸው እና እድገት የማግኘት አድላቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።

ከሚከፈልበት  ሥራ በተጨማሪ ሴቶች አብዛኛውን የማይከፈልበት ሥራ ይሰራሉ። በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2013 በቀን ውስጥ ወንዶች 6.6% ሴቶች ደግሞ 19.3% ሚሃል ጊዜያቸውን የማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራዎችን ይሰሩ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2019 መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ሴቶች ከወንዶች 2.9 እጥፍ ደሞዝ በማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ(የአለም ባንክ)። ፆታን መሰረት ያደረገ የስራ ክፍፍል ለያልተመጣጠነ የስራ እድሎችንና ላጋደለ የሀብት ቁጥጥር  አስተዋፅኦ ያደርጋል። ይሁን እንጂ በብሔራዊ ስሌት ውስጥ በቤት ውስጥ የሴቶችን ያልተከፈለ ሥራ ዋጋ ለማስላት ብዙም ጥረት አልተደረገም።

በማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራዎች ላይ ያለው የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት የሴቶችን ዕድል በሚቀንስ በአድሎአዊ ደንቦች ተብራርቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ፣ የሚከፈልበት ሥራ እንደ ወንድ ተግባር ሲቆጠር፣የማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራ ደግሞ እንደ የሴቶች ኃላፊነት ይቆጠራል (ገለታ እና ሌሎች፣ 2015)። ወንዶች የቤት ውስጥ ሥራዎችን ሲሠሩ “ሴቶችን እንደሚረዷቸው” ይሰማቸዋል እንጂ እንደ የእነሱ እኩል ኃላፊነት አይቆጥሩትም። ማንበብና መጻፍ እና ትምህርት ለሴቶች ማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራ ኃላፊነት ሚና ተጠያቂ አይደሉም። የመንከባከብ ሀላፊነት አለመመጣጠን በሀብታሞች እና በተማሩ ሀገራት ውስጥም አለ፣ሴቶች  የገቢ እና የትምህርት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን  ከ60% በላይ ጊዜያቸውን ለቤት ስራ እና ህጻን እንክብካቤ ነው የሚያውሉበት(Rizavi and Sofer, 2010)። ማህበራዊ ደንቦች የሴቶችን እና የልጃገረዶቺን የመደራደር አቅምን ሊያዳክሙ የሚችሉት ‘የውጭ አማራጮቻቸውን’ በማዳከም ወይም የበለጠ ‘ዝምተኛ’ እና ‘ስውር’ ባህሪን ለሴቶች በመወሰን ነው። ሰዎች ለእነሱ የማይጠቅም ሁኔታን እንዲቀበሉ ስለሚያደርጉ ማህበራዊ ደንቦች እና የድርድር ሂደቶች በቅርበት የተያያዙ ናቸው።

ስለዚህ ማህበራዊ ደንቦችን እንዴት መቀየር ይቻላል?

ብዙ ፈተናዎች ቢያጋጥሟትም ኢትዮጵያ በስርዓተ ጾታ ልዩነት ደረጃ ከፍ ብላለች።  እ.ኤ.አ 2021 ኢትዮጵያ በሴቶች አቁልነት መለኪያ ከኬንያ አንክዋን በመብለጥ ከ146 አገራት 74ኛ ደረጃ ላይ ተመድባለች።እ.ኤ.አ. ከ2010 ጀምሮ በኢትዮጵያ ያለው የስርዓተ-ፆታ ልዩነት እየጠበበ የሄደው በሴቶች የተያዙት የፓርላማ መቀመጫ በመጨመሩ ነው። እ.ኤ.አ. በ2022 ሴቶች 41.5% የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፓርላማ መቀመጫ ነበራቸው።

ደንቦችን ለመለወጥ የተለያዩ መንገዶች አሉ። አንዳንድ ጊዜ ግን ለመቀየር ያስቸግራል፤ምንም እንኳን ሰዎች በተለመደው ደንብ ባያምኑም። በኢትዮጵያ ጉዳይ አዲስ አስተዳደር ለሴቶች በፓርላማ ኮታ አዘጋጅቷል። ይህም ማህበረሰቡ ቀደም ሲል ከአመራር እድሎች የተገለሉ ብቁ እና የተማሩ ሴቶች እንዳሉ እንዲገነዘብ አግዟል። በአመራር ቦታዎች ላይ ያሉ የሴቶች ጥቅሞች ለትውልድ ትውልድ መሪ ለመሆን በሚመኙ ወጣት ልጃገረዶች ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ይኖረዋል። ተመጣጣኝ ያልሆነ የሥርዓተ-ፆታ ደንቦችን ለመለወጥ አርአያ በቦታ ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው።

ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በኢትዮጵያ አንዳንድ የስርዓተ-ፆታ ለውጦችን እያሻሻለ ቢሆንም በበቂ ፍጥነት አይደለም። ሴቶች በማደግ ላይ ባሉ ገበያዎች ውስጥ በበቂ ሁኔታ ባለመዋሃዳቸው የኢኮኖሚ እድገት ያጣሉ። እንደ ኮታ ማዘጋጀት እና የልጃገረዶች እና የሴቶች ፍላጎቶች ላይ ማነጣጠር ያሉ ተነሳሽነት  ለአመታት ያመለጡ እድሎች ዳግም ማስጀመር ይጠበቅባቸዋል። ለምሳሌ ላገቡ ሴቶች አገልግሎት ማሻሻል፣ ከጥቃት እና ከስርቆት ነፃ በሆኑ ቦታዎች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እና ወንዶች እና ወንዶች ልጆች በአዎንታዊ ተግባራት ላይ ማሳተፍ ያልተመጣጠኑ የሥርዓተ-ፆታ ደንቦችን ለመፍታት ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸው የፖሊሲና የፕሮግራም መፍትሄዎች ናቸው (ብርሃኔ እና ሌሎች፣ 2019)። አንዳንድ ሌሎች ምክሮች እነሆ፡-

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች፡– ሴቶች በማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራዎች ላይ የሚያሳልፉት ጊዜ ወሳኝነትና በገንዘብ ቢተመን ለኢኮኖሚው ምን ይሃል አንደሚያበረክት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማካሄድ።

ከእንክብካቤ ጋር የተያያዘ የንግድ ሥራ ልማት፡- የሥራ አካባቢን ለማሻሻል እና የሚሰሩ እናቶችን አሰራር ለማሳደግ የመዋዕለ ሕፃናት ተቋማትን መገንባት።

ጣልቃ-ገብነት፡- ልማታዊ ተዋናዮች እና ፖሊሲ አውጪዎች በማስረጃ የተመሰረቱ መፍትሄዎች መስፋፋታቸውን ለማረጋገጥ አወንታዊ እርምጃ፣ ኢላማዎች፣ ኮታዎች እና ሌሎች የሚገመገሙ ስልቶችን መደገፍ አለባቸው።

ማህበራዊ ደንቦችን የመረዳትና በነሱ የመነጋገር ወሳኝ አስፈላጊነት ላይ ትኩረት እየጨመረ መጥቷል። ቀዳሚዎቹ የማህበራዊ ደንቦች በሚወጡት ፖሊሲዎች፣ በተመደቡት ሀብቶች፣ በሚደረጉ ውሳኔዎች እና መንግስታት እና ድርጅቶች በሚከተሏቸው እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አላቸው።

ጤናማ እና  ፍትሃዊ የሆኑ ማህበረሰቦችን መፍጠር ለሚፈልጉ፣ እባክዎ

  • ለአጋርነት ለማካተት ይፃፉልን፡ [email protected]
  • ለዚህ ብሎግ ምላሽዎን ከዚህ በታች ያካፍሉ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ማህበራዊ ደንቦችን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነ ያሳውቁን

እውቅና

ይህ ፅሁፍ በእድገት እና ኢኮኖሚያዊ እድሎች ለሴቶች (GROW) – የምስራቅ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ ስር ከነበረው ፕሮጀክት ያገኘነውን ትምህርት ለማንፀባረቅ ካዘጋጀናቸው ተከታታይ ፅሁፎች የመጀመሪያው ነው። GrOW በአለም አቀፍ የልማት ጥናትና ምርምር ማዕከል (IDRC)፣ በቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን እና በዊልያም እና ፍሎራ ሄውሌት ፋውንዴሽን የተደገፈ ነው። ይህንን ፕሮጀክት ‘የሴቶችን ኢኮኖሚ ማጎልበት (WEE) እና ያልተከፈለ እንክብካቤን (UC)’ በኢትዮጵያ እንዲቋቋም ስላደረገው GrOW ከልባችን እናመሰግናለን። እንዲሁም ለአጋሮቻችን ምስጋናችንን እናቀርባለን; WISE የፖሊሲ ተዋናዮችን አቅም ለማጠናከር ላደረጉት ጥረት እና አዲስ ፓወር ሃውስ በሀገር ውስጥ የWEE ሻምፒዮናዎችን ጥምረት በማጠናከር ላይ ለሰሩት ስራ።

Reference

  1. Berhane, Y., Worku, A., Tewahido, D., Fasil, N., Gulema, H., Tadesse, A. W., & Abdelmenan, S. (2019). Adolescent Girls’ Agency Significantly Correlates With Favourable Social Norms in Ethiopia—Implications for Improving Sexual and Reproductive Health of Young Adolescents. Journal of Adolescent Health, 64(4), 52-59
  2. Bicchieri, C. (2017). Norms in the Wild: How to Diagnose, Measure, and Change Social Norms. Oxford: Oxford University Press. 
  3. Geleta, D., Birhanu, Z., Kaufman, M., & Temesgen, B. (2015). Gender norms and family planning decision-making among married men and women, Rural Ethiopia: A qualitative study. Science Journal of Public Health, 3(2), 242 – 250.
  4. Statista website: Gender gap index in Ethiopia in 2022, by sector. Retrieved on 1/9/23 from: https://www.statista.com/statistics/1253877/gender-gap-index-in-ethiopia-by-sector/ 
  5. The World Bank.  Gender Data Portal: Proportion of women who have ever experienced any form of sexual violence (% of women age 15-49). Retrieved on 1/9/23 from: https://genderdata.worldbank.org/indicators/sg-vaw-afsx-zs/
  6. Rizavi, S. S. and C. Sofer (2010), “Household Division of Labour: Is There Any Escape From Traditional Gender Roles?”Cahiers de la Maison des Sciences Economiques, L’Atelier Paris1-Le Caire, Cairo.
Tags:
Leave A Comment

Skip to content