በኢትዮጵያ የሴቶችን የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ እውቅና አለመስጠት ያስከተለው ጉዳት

በሂዳያ ሙሂደን እና ክሪስቲ ድሩክዛ 

የግለሰቦች እና የህብረተሰቡ አጠቃላይ ደህንነት በሁለቱም በሚከፈልባቸው እና በማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራዎች ላይ የተመሠረተ ነው። አንዳንድ እንደ ከልጆች ጋር ጊዜ ማሳለፍ ወይም እራት ማብሰል ያሉ ተግባራት ከሌሎቹ የበለጠ አስደሳች ሊሆኑ ቢችሉም ሁሉም ተግባራት የበለፀገ እና ጤናማ ማህበረሰብን ለመጠበቅ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። የማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራዎች እንደ ምግብ ማብሰል፣ ማጽዳት፣ ውሃ መቅዳት እና ማገዶ መሰብሰብ በተጨማሪም ህጻናትን ወይም አዛውንቶችን መንከባከብ ስራዎችን ያካትታሉ። እነዚህ የቤት ውስጥ ኃላፊነቶች ለጤናማ ማህበረሰብ እና ኢኮኖሚ ወሳኝ ናቸው፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ዋጋቸው ከሚገባው በታች የተገመተ ነው። ሴቶች እና ልጃገረዶችም እነዚህን ሀላፊነቶች በብዛት ይሸከማሉ። በ ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት እ.ኤ.አ 2019 ሪፖርት መሠረት፣ ሴቶች ሦስት አራተኛውን  የማይከፈልባቸውን  የቤት ውስጥ ስራዎች ፣ ወይም ከ 75 በመቶ በላይ ከተወሰነው አጠቃላይ ሰዓታት የሚሆኑትን ይሰራሉ ፤ ይህም በአማካይ ከወንዶች 3.2 እጥፍ ይበልጣል። የሴቶች የማይከፈልባቸው  የቤት ውስጥ ስራዎች በአብዛኛው በፖሊሲ አጀንዳዎች እና ኢኮኖሚያዊ ሰሌቶች ላይም ዋጋ አይሰጠውም።

የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ በሴቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። ይህም ለተከፈለ ሥራ እና ትምህርት ጊዜን እና ግብዓቶችን ይቀንሳል። ይህ ደግሞ በሠራተኛ ኃይል እና በደመወዝ ውስጥ የጾታ ልዩነት እንዲኖር ያደርጋል በተለይም  ከፍተኛ ደመወዝ በሚከፈልባቸው ስራዎች፣ በጡረታ ክፍያ እና በአመራር ሚናዎች ላይ ግልጽ የሆነ ክፍተት አለው።  ሴቶች ለማይከፈልባቸው የቤት ውስጥ ስራዎች ከወንዶች ሦስት እጥፍ የሚበልጥ ጊዜ ቢሰጡም፣ በአለም አቀፍ 35% የሚሆኑ ሴቶች በደመወዝ ተቀጥረው  የሚሰሩ ናቸው(OECD፣ እ.ኤ.አ 2014)። ነገር ግን፣ የሴቶች ሥራ በብሔራዊ  የጉልበት አተረጓገም ውስጥ ሙሉ በሙሉ እውቅና አልተሰጠውም (አድማሱ እና ሌሎች፣ እ.ኤ.አ 2021)።

ልጃገረዶች እና ሴቶች ገዳቢ የሆኑ የስርዓተ-ፆታ ደንቦችን እና ኢኮኖሚያዊ ኢፍታዊነት እየታገሉ ሳሉ የድህነት ተፅእኖ ደግሞ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች የበለጠ ያባብሰዋል።  ሴቶች እና ልጃገረዶች በቤት ውስጥ የእንክብካቤ ስራዎችን ሃላፊነት ሲወስዱ፣ የትምህርት እና የስራ የመከታተል እድላቸው ይቀንሳል። በተለይም  ለተሻለ  ወደፊት  ውስን   እድል ላላቸው  በገጠር ላሉ ወጣት ሴቶች ከድህነት ማምለጥ የበለጠ ከባድ ይሆናል። ከኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢ ብዙ ወጣት ሴቶች የቤት ሰራተኛ ሆነው ለመስራት ወደ ከተማ እየፈለሱ ነው። በገጠር ማህበረሰቦች የሚገኝ እኩልነት እና አቅም አለመኖር ሁኔታ እነዚህ ሴቶች የተሻለ ዕድሎችን ለመፈለግ ወደ ከተማ ማእከላት እንዲሰደዱ ያደርጋቸዋል (አድማሱ እና ሌሎች፣ እ.ኤ.አ 2021)። የወጣት ሴቶች የስራ እድል ከወጣት ወንዶች ጋር ሲነጻጸር አሁንም ውስን ነው።

ያለ ዕድሜ ጋብቻ ሴቶች የሚከፈልበት የጉልበት ሥራን እንዲተዉ የሚያደርጋቸው ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ቀጥሏል። የከተማ ወይም የገጠር መኖሪያ፣ ትምህርት፣ የኑሮ ደረጃ፣ ልማዶች እና ደንቦች በጋብቻ ውስጥ የወጣት ሴቶችን የመደራደር አቅም ለመቅረጽ አብረው ይሰራሉ። የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ  ሸክም የሴቶችን ኢኮኖሚ ደህንነት ላይ ብቻ ሳይሆን የግል እድገታቸውን እና የስልጣን እድላቸውን ይቀርፃል። ደጋፊ ፖሊሲዎችን በመተግበር ሴቶችን በመንከባከብ ረገድ ያላቸውን ወሳኝ ሚና በመገንዘብ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማጎልበት እና ሁሉንም ያካተተ ማህበረሰብ ለመፍጠር ወሳኝ ነው። ስለዚህ የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ  ሀላፊነቶችን እኩል ያልሆነ ክፍፍል በመፍታት የሴቶችን ሙሉ አቅም በማጎልበት እና በሁሉም የሕይወት ዘርፎች እንዲበለጽጉ አስፈላጊውን ድጋፍ ልናደርግላቸው እንችላለን።

ወጣት ሴቶች በገጠር ጥሩ ስራ የማግኘት እድል አሁንም በጣም ውስን ነው፤ ያገኙትም ጥሩ የስራ ሁኔታ፣ ዝቅተኛ ክፍያ ወይም ከትምህርታቸው እና ከስልጠናቸው ጋር ያልተያያዙ ስራዎች ናቸው ስለሚሆኑ እንዲያማርሩ ያደርጋቸዋል። ለገጠር ወጣት ሴቶች  ወደ ከተማ ሄዶ የቤት ሰራተኛ መሆን እና በምሽት ትምህርታቸውን መቀጠል አቅማቸውን ለማጎልበት ወሳኝ ስልት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በገጠር ያሉ ወጣት ሴቶች ጥሩ የስራ የማግኘት እድላቸው ውስን በመሆኑ አንደ ወንዶች አቻዎቻቸው ተቀጥሮ የመስራት ዕድላቸው አነስተኛ ነው።

ትምህርት እና ሥራ ወደ የላቀ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ ለመድረስ ወሳኝ መንገዶች ናቸው። ልጃገረዶች እና ሴቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ላላችው እኩል ያልሆነ ደረጃ ኢኮኖሚያዊ አለመመጣጠንን እንደ ዋና የችግራቸው መንስኤ  አድርገው ይመለከቱታል  ። ሆኖም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሴቶች እና ልጃገረዶች የትምህርት እና የስራ እድሎች የተገደቡ በመሆናቸው የጥገኝነት ዑደት በመፍጠር ለማምለጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል።

ማጠቃለያ

በአጠቃላይ  የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ በሴቶች ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ጥልቅ እና ዘርፈ ብዙ ነው። የእንክብክቤ ሃላፊነት ክፍፍል እኩል አለመሆን ሴቶች የሚከፈላቸው ሥራ እና ትምህርት እንዳያገኙ ትልቅ እንቅፋት ይፈጥራል። የሥርዓተ-ፆታ ልዩነቶችን በሠራተኛ ኃይል እና በደመወዛቸው ውስጥም እንዲቀጥል ያደርጋል። ድህነት እና ገዳቢ የስርዓተ-ፆታ መመዘኛዎች  የእኩልነት መጓደልን  በተለይም  ወጣት ሴቶች ጥሩ የስራ እድል እና የተሻለ የወደፊት እድሎች በማያጋጥሟቸው የኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች  የበለጠ ያባብሱታል።

አንድ ብቸኛ ፋይዳዊ መፍትሄ ባይኖርም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሴቶች እኩልነት አለመመጣጠን የረዥም ጊዜ አካሄድ አሁንም ያስፈልጋል። የሚከተሉት ነጥቦች ለየማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ እንደ መፍትሄዎች ይመከራሉ.

  • በብሔራዊ መለያዎች ስርዓት ጥቅም ላይ በሚውለው የጉልበት  አተረጓገም ውስጥ የሴቶች ሥራ እውቅና እንዲሰጠው ማድረግ
  • የቴክኒክ እና የሙያ ስልጠና የምስክር ወረቀቶችን እና እድሎችን ጨምሮ በገጠር ያሉ ሴቶች የትምህርት ቤት ወደ ሥራ ሽግግርን ማሻሻል።
  • ስለ ጾታ ልዩነት አመታዊ ሪፖርት ማድረግ እና ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያን ማበረታታት።
  • ከወንዶች ጋር ሲነፃፀሩ ዝቅተኛ ክፍያ የሚከፍል ከፍተኛ ደረጃ ያለው ድርጅት ፍርድ ቤት መክሰስ 
  • ሴቶች ለወሊድ ፈቃድ የሚያገኙትን እኩል የአባትነት ፈቃድ ለወንዶች መስጠት
  • ሴቶችን እንደ እናቶች ብቻ እውቅና ከመስጠት ይልቅ እንደ ንግድ ባለቤቶች እና መሪዎች አርአያ የሚሆኑ ሴቶችን መደገፍ።
  • በገጠር ውስጥ የሴቶችን ሥራ ፈጣሪነት እና የምርት ልማትን መደገፍ 
  • በፀሃይ ፓኔል የሚሰሩ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖችን እና ሌሎች  የኤሌክትሪክ ኃይል የማያስፈልጋቸው የሰው ኃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ለምሳሌ የእጅ ውሃ ፓምፖችን ማከፋፈል
  • የቤት ሰራተኞችን መብቶች መጠበቅ እና ዝቅተኛውን ደመወዝ መጠን መጨመር

እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እና የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማሳደግ   የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራን እውቅና መስጠት, መቀነስ እና እንደገና ማከፋፈል አስፈላጊ ነው። በቤተሰብ እና በማህበረሰቦች መካከል ፍትሃዊ የስራ ክፍፍል እና ጠቃሚ የህዝብ አገልግሎቶች አቅርቦት ሴቶች የመንከባከብ ኃላፊነታቸውን ከሌሎች የሕይወት ዘርፎች ጋር ማመጣጠን ያስችላቸዋል። እነዚህን እርምጃዎች በመተግበር የሴቶችን በመንከባከብ ሚናዎች ውስጥ የሚያበረክቱት አስተዋፅዖ የሚከበርበት እና የሚደገፍበት ማህበረሰብ መፍጠር እንችላለን።

የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራን እውቅና መስጠት እና መቀነስ ለበለጠ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት፣ የተሻሻለ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎች እና ለሴቶች  ማጎልበት መንገዱን ይከፍታል። ሴቶች በሁሉም የሕይወት ዘርፎች የሚበለፅጉበት የበለጠ ፍትሃዊ እና አካታች ዓለም ለመገንባት በጋራ እንስራ።

እውቅና

ይህ ፅሁፍ በእድገት እና ኢኮኖሚያዊ እድሎች ለሴቶች (GROW) – የምስራቅ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ ስር ከነበረው ፕሮጀክት ያገኘነውን ትምህርት ለማንፀባረቅ ካዘጋጀናቸው ተከታታይ ፅሁፎች የመጀመሪያው ነው። GrOW በአለም አቀፍ የልማት ጥናትና ምርምር ማዕከል (IDRC)፣ በቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን እና በዊልያም እና ፍሎራ ሄውሌት ፋውንዴሽን የተደገፈ ነው። ይህንን ፕሮጀክት ‘የሴቶችን ኢኮኖሚ ማጎልበት (WEE) እና ያልተከፈለ እንክብካቤን (UC)’ በኢትዮጵያ እንዲቋቋም ስላደረገው GrOW ከልባችን እናመሰግናለን። እንዲሁም ለአጋሮቻችን ምስጋናችንን እናቀርባለን; WISE የፖሊሲ ተዋናዮችን አቅም ለማጠናከር ላደረጉት ጥረት እና አዲስ ፓወር ሃውስ በሀገር ውስጥ የWEE ሻምፒዮናዎችን ጥምረት በማጠናከር ላይ ለሰሩት ስራ።

References

  1. Admasu, Y., Crivello, G., & Porter, C. (2021). Young women’s transitions from education to the labour market in Ethiopia. A gendered life-course perspective,” WIDER Working Paper, 96.
  2. ILO (2019) “The Unpaid Care Work and the Labour Market. An analysis of time use data based on the latest World Compilation of Time-use Surveys/Jacques Charmes; International Labour Office, Geneva. 
  3. OECD Development Centre (2014) “Unpaid Care Work: The missing link in the analysis of gender gaps in labour outcomes”
Tags:
Leave A Comment

Skip to content