የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራዎችን የሚመለከቱ ድምጾች፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የወንዶች፣ የሴቶች እና የወጣቶች ግንዛቤ ዳሰሳ

“የዓለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ ዋጋ ከአለም አቀፉ የሀገር ውስጥ ምርት እስከ 9 በመቶ (11 ትሪሊዮን ዶላር) ይደርሳል ብሎ ይገምታል፣ የሴቶች አስተዋፅኦ 6.6 ከመቶ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ውስጥ ሲሆን የወንዶች ደግሞ 2.4 በመቶ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ነው።

(ሄርናንዶ፣ እ.ኤ.አ 2022)

በዶ/ር ክሪስቲ ድሩክዛ፣ ዶ/ር አሚራ ካዱር እና ሂዳያ ሙሂደን

 

መግቢያ

በቤተሰብ ውስጥ የሚደረጉ ከገበያ ውጪ ያሉ የማይከፈልባቸው ተግባራት ሁሉ  የቤት ውስጥ ስራዎች ይባላሉ። ይህ ቀጥትኛ አንክብካበን እንደ ህጻናትን ወይም አረጋውያንን መንከባከብ እና ቀጥተኛ ያልሆነ እንክብካቤን፣እንደ ምግብ ማብሰልን፣ ማጽዳትን ወይም ውሃ መቅዳትን ያካትታል (OECD፣ እ.ኤ.አ 2019)። ያልተከፈለ ስራ መጠን እና ተጽእኖ ለሴቶች እና ለወንዶች ይለያያል፣ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች እንደ የቤተሰብ ገቢ፣ የትምህርት ደረጃ፣የጋብቻ ሁኔታ እና የልጆች ቁጥር ሁሉም እንደዚህ ባሉ ልዩነቶች ውስጥ ሚና ይጫወታሉ (ILO, እ.ኤ.አ 2018)። በአለም ዙሪያ ያሉ ሴቶች እና ልጃገረዶች አብዛኛዎቹን ያልተከፈለ እንክብካቤ እና የቤት ውስጥ ስራዎችን ያከናውናሉ።

በቤት ውስጥ ኢኮኖሚ  የህፃናት ሚና ፣የቤት ውስጥ ስራ ምደባን እድገት እና በሴቶች እና በወንዶች ሥራ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል። ኢትዮጵያዊያን ልጃገረዶች  የጾታ ክፍፍል ባለበት ባህል ውስጥ ስላደጉ ሴት በመሆናቸው ብቻ ከነሱ የሚጠበቁ  የተወሰኑ ባህሪያት አሉ (crivello et al., እ.ኤ.አ 2019)። የቤት ውስጥ ሥራዎችን ገና በለጋ ዕድሜያቸው መማር ይጀምራሉ፣ እነዚህም በተደጋጋሚ በጾታ ሚናዎች እና በቤተሰብ እና በማህበረሰቦች ውስጥ ባሉ መከፋፈል ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የቹታ እና ሞሮው ጥናት (እ.ኤ.አ 2015) ልጃገረዶች እና ሴቶች ሌሎችን ለመንከባከብ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉ አረጋግጧል። ይህ ሥራ ክፍያ የሌለው ብቻ ሳይሆን ብዙውን ጊዜ እንደ ሥራ እንኳን አይቆጠርም። ይህ በሴቶች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አለው። ጾታ እና ማህበራዊ ሚናዎች ምርጫቸውን እና ጊዜን በመገደብ ደካማ ያደርጋቸዋል።

 

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የ”እናትነት” ሚና መቀየር: ስለማየከፈልበት እንክብካቤ ሥራ  ሴቶች ምን ያስባሉ?

በገጠር ማህበረሰብ ውስጥ ያለው የሥርዓተ-ፆታ ሚና የሴቶችን ምርጫ ይገድባል, ይህም  የማይከፈልበት  የቤት ውስጥ እና የመራቢያ ተግባራት የጊዜን ድህነትን ያስከትላል, ይህም በሴቶች ኢኮኖሚያዊ እድሎች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አለው። ሴቶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በእርሻ ሥራ ላይ ሲሆን አብዛኛውም ያልተከፈለ የቤተሰብ ኃላፊነት ነው። ኬና (እ.ኤ.አ. 2019) የመደራደር አቅም ማነስ ለሴቶች የመረጃ ተደራሽነት እና አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ውስንነት  ምክንያት መሆኑን አመልክቷል።

ነገር ግን፣ የአሁን ወጣት ሴቶች በት/ቤት ረዘም ያለ ጊዜ ያሳልፋሉ ይህም ወደ ጉርምስና ሽግግራቸውን ያዘገየዋል ።

“በእኛ ግዜ ወላጆች ገና በልጅነታቸው ሴት ልጆቻቸውን ለባሎቻቸው ይሰጡ ነበር አሁን ግን ሁሉም ነገር በልጃገረዶች ምርጫ ላይ የተመሰረተ ነው”።

የአዛዉንት  እናት አስተያየት (ከክሪቬሎ እና ሌሎች፣ እ.ኤ.አ 2019)

እነዚህ እድገቶች ለወጣት ሴቶች የሥርዓተ-ፆታ ለውጥ ያመለክታሉ። ከልጅነት ትምህርት እስከ አዋቂ ሥራ፣ ጋብቻ እና እናትነትንባሉ የሕይዎት ደራጃዎች ላይ አዲስ መንገድ ይቀዳሉ።

ስለ የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራዎችን ወጣቶች ምን ያስባሉ?

ኢትዮጵያ ውስጥ ልጆች በቤተሰብ ኢኮኖሚ ላይ ማዕከላዊ ሚና ይጫወታሉ። ማህበራዊ አድሏዊነት፣ ኢኮኖሚያዊ አቋም፣ የሴቶች እና የወንዶች የትምህርት እድሎች አመለካከቶች እና ባህላዊ የቤተሰብ ውሳኔ አሰጣጥ ሁሉም ለጾታ አለመመጣጠን አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። የቤተሰብ ቅንብር፣ የትውልድ ቅደም ተከተል እና የእህት- እህት ቅንብር የትኞቹ ልጆች የትኛውን ስራ እንደሚሰሩ ይወስናሉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ከሌሎቹ የበለጠ ከባድ ሸክም አላቸው።

በክሪቬሎ እና ሌሎች፣ 2019 በተደረገ ጥናት፣ የደንቦች ተፅዕኖ በልጃገረዶች እና በቤተሰቦቻቸው ውስጥ እየጨመሩ መሄዳቸውን አረጋግጧል። ስለዚህ ወጣት ሴቶች ከእናቶቻቸው ይልቅ ወደ ጉልምስና በሚወስዱት መንገድ ላይ ብዙ አማራጮች ቢኖራቸውም፣ ራሳቸውን ችለው ውሳኔ የመወሰን ችሎታቸው ተገድቧል። ምክንያቱም ወጣቶች በባህላዊ እና በዘመናዊ ህይወት፣ በድህነት እና በተስፋ መካከል ስለሚያዙ ስለህይወት ምርጫቸው እርግጠኛ እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል።

ትምህርት እና የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት የወጣት ሴቶችን ማጎልበት እና ምርጫ ማድረግ የወቅቱ የልጅነት ወሳኝ አካላት ናቸው ነገርግን እነዚህን ግቦች ማሳካት ከባድ ነው። ምንም እንኳን በልጃገረዶች የወደፊት እጣ ፈንታ እና የትምህርት ስኬት ብዙ የሚጠበቁ ነገሮች ቢኖሩም፣ እነዚህ ግን በሚኖሩበት አካባቢ ባለው እውነታ የተገደቡ ናቸው። ኃላፊነትን የመሸከም ግዴታቸው ከትልቅ የቤት ውስጥ ችግሮች ለምሳሌ ድህነት እና እጦት ጋር የተያያዘ ነው። ይህ ብዙውን ጊዜ ትልቋ ሴት ልጅ ወላጆቻቸው የሚከፈልበት ሥራ ሲፈልጉ ሌሎች ልጆችን የመንከባከብ እና የቤት ውስጥ ሥራዎችን የመስራት ሃላፊነት ይተውላታል ። ከዚህም በላይ ስደት በገጠር ወጣቶች ዘንድ ወደ ጉልምስና ማድግ ት/ቤትን ትቶ ወደ ሥራ የመጀመሪያ ሽግግር ተደርጎ ይወሰዳል።

የቅርብ ጊዜ ግኝቶች ወጣት ባለትዳር ሴቶች በቀን እስከ 8 ሰአታት ደሞዝ በማይከፈልበት ስራ እና እንክብካቤ ያሳልፋሉ ይላል። ይህም የግትር የስርዓተ-ፆታ ደንቦችን ተፈጥሯዊነት የሚያንፀባርቅ ሲሆን ይህም ለወንዶች የቤት አስተዳዳሪነት እና ለሴቶች ተንከባካቢነት ሚና ይሰጣል። ወጣት እናቶች ወንዶች የመወሰን ስልጣን እንዳላቸው እና ሴቶች ጨዋ እና ታዛዥ መሆን እንዳለባቸው ተከራክረዋል (crivello et al., 2019)። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በጥናቱ ውስጥ ያሉ ሌሎች ወንዶች በህጻን እንክብካቤ ላይ ‘የማይጠቅሙ’ ናቸው ብለዋል (crivello et al.፣ 2019)። የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት በሁሉም ሰው አመለካከት እና እምነት ላይ ተፅዕኖ አለው።

 

ወንዶች ስለ የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራዎችን ምን ያስባሉ?

በወንዶች እና በሴቶች መካከል የሚስተዋለውን ያልተመጣጠነ የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራዎችን መፍታት የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማምጣት ወሳኝ እርምጃ ነው። የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራዎችን ብዙውን ጊዜ እንደ ሁለተኛ ደረጃ ጉዳይ ይታያል ነገር ግን የስርዓተ-ፆታ አለመመጣጠን ዋነኛ መንስኤዎች አንዱ ነው። ምንም እንኳን ያልተከፈለ የእንክብካቤ ስራ እኩል ያልሆነ ሸክም እውቅና መስጠት አስፈላጊ ቢሆንም የሴቶችን መብት ሁኔታ ለመለወጥ በቂ አይደለም። ሴቶችን፣ ቤተሰባቸውን እና ማህበረሰቦችን ለማብቃት፣ ሴቶች ላልተከፈለ እንክብካቤ ስራ የሚያጠፉት ጊዜ መቀነስ እና እንደገና መከፋፈል አለበት። ይህም ማለት ወንድ ዘመዶች በተለይም ባሎች አንዳንድ ሸክሙን መሸከም አለባቸው ማለት ነው።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ወንዶች ለሴቶች ያላቸው አመለካከት በቅርብ ጊዜ ተለውጧል; ለምሳሌ በደቡብ ኢትዮጵያ በወላይታ ሶዶ ከተማ በዘውዱ ቢ እና ሌሎች (2021) የተደረገው ጥናት ባለትዳር ወንዶች ጾታን መሰረት ባደረገ የጉልበት ድልድል ላይ ያላቸውን አመለካከትና ለትዳር አጋሮቻቸው የቤት ውስጥ ሥራዎችን የመመደብ ልምድ በመፈተሽ የወንዶች አመለካከትና ተግባር ለውጥ እንዳለ ተረጋግጧል። ምላሽ ሰጪዎች አዎንታዊ የፆታ ግንኙነት እና የቤተሰብ ሚና አቅጣጫዎች ነበራቸው። ግኝቶቹ እንደሚያሳዩት አብዛኞቹ (86.1%) የቤት ውስጥ ሥራዎችን ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር እንደሚካፈሉ እና የሥርዓተ-ፆታ የስራ ክፍፍልም እንዲሁ እየተቀየረ ነው። የትምህርት, እና የሃይማኖት መሪዎች, አርአያ እና ወንድ ዘመዶች ድጋፍ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ።

ወጣት እናቶች የወንዶችን የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ ድርሻ ጨምሮ የማይመለከቱ ከሆነ፣ ምናልባት ወንዶች የትዳር አጋሮቻቸው ምን ያህል የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራዎች እንደሚሰሩ አያውቁም። በወንዶች እንክብካቤ ውስጥ መዋቀራዊ-ደረጃ ለውጦችን ማድረግ በሁለት ምክንያቶች አስቸጋሪ ነው; በመጀመሪያ፣ ፖሊሲ፣ ምርት እና ህዝባዊ ህይወት በወንዶች ቁጥጥር ስር ነው፣ ሁለተኛም፣ አባታዊ ስርዓት በቤት ውስጥ የወንዶችን ዝቅተኛ ተሳትፎ ይደግፋል። የእንክብካቤ ዋጋን እንደ ማህበረሰብ መርህ ማሳደግ ሁለቱንም ጉዳዮች በአንድ ጊዜ ይፈታል፣ በተለይም እንክብካቤ ከፆታ ጋር ያለውን ቁርኝት መፍታት አስፈላጊ ነው። ወንዶችን ተጠያቂ በማያረጋቸው አባታዊ ስርዓት ውስጥ የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ ድርሻቸውን እንዲሠሩ እንዴት ማበረታቻ ይቻላል?

ማጠቃለያ

የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ ተጨማሪ ጊዜ የሚያሳልፈው ጊዜ የሚከፈልበት ስራ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ፣ ራስን መንከባከብ፣ እረፍት፣ ትምህርት እና መዝናኛ ጊዜ ያነሰ ይሆናል። ከባድ እና እኩል ያልሆነ የእንክብካቤ ሀላፊነቶች ሴቶች የመማር፣ የተስተካከለ የስራ፣ የጤና እና የመሳተፍ ወዘተ መብቶቻቸውን እኩል እንዳያገኙ ገዳቢ እና ለስርዓተ-ፆታ እኩልነት ትልቅ እንቅፋት ነው።

የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ ድርሻቸው ምክንያት፣ ሴቶች በኢኮኖሚ አድገት  ውስጥ ሙሉ በሙሉ መሳተፍ አይችሉም። የሚከፈልበት ሥራ ለማግኘት ብዙ ጊዜ የእረፍት ጊዜያቸውን መስጠት አለባቸው, እና ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ ሥራ ለማግኘት አስቸጋሪ ነው።ይህም ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ትልቅ እንቅፋት ነው።

በኢትዮጵያ ያለውን ያልተመጣጠነ  የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ ጫና ለመቋቋም የሚከተሉትን ነጥቦች ይመከራል:

  1. ያልተከፈለ የቤት ውስጥ እና የእንክብካቤ ስራ አስፈላጊነት እና ከልማት ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ የህዝብ ግንዛቤን በመጨመር  የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራ ላይ ግልፅ ትኩረት እንዲሰጠው ማድረግ። የሚዲያ ተሳትፎ እና የግንኙነት ዘመቻዎች  የማይከፈልበት የቤት ውስጥ ስራን ለመቀነስ እና እንደገና ለማከፋፈል የፖሊሲ ቅስቀሳዎች ያስፈልጋሉ::
  2. የወንድ ተሳትፎን በማጎልበት ማህበራዊ ደንቦችን መቀየር እና የእንክብካቤ ሃላፊነቶችን እንደገና ማከፋፈል; ይህ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማግኘት አስፈላጊ ነው::
  3. የተሻለ የስራ እና የህይወት ሚዛንን ለማራመድ የህጻናት እና አረጋውያንን እንክብካቤ የተሻለ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ማዳበር።

የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም በኢትዮጵያ ለማስፋት በወንዶች እና በሴቶች መካከል በቤተሰብ እና በስራ ቦታ የእንክብካቤ ስራ እንዴት ዋጋ እንደሚሰጥ፣ እንደሚመደብ እና እንደሚጋራ ላይ ለውጦች አስፈላጊ ናቸው።

References

  1. Chuta, N. and Morrow, V. (2015) “Young Lives Working Paper 135. Youth Trajectories through Work and Marriage in Rural Ethiopia,” Young Lives [Preprint]. Available at: http://r4d.dfid.gov.uk/pdf/outputs/YoungLives/YL-WP135-Youth-Trajectories-in-Ethiopia.pdf.
  2. Crivello, G., Boyden, J. and Pankhurst, A. (2019) “‘Motherhood in Childhood’: Generational Change in Ethiopia,” Feminist Encounters, 3(1–2).
  3. Hernando, R. C. (2022) ”Unpaid Care and Domestic Work: Counting the Costs, APEC Policy Support Unit.
  4. ILO. (2018) ”Women do 4 times more unpaid care work than men in Asia and the Pacific”. Available at: https://www.ilo.org/asia/media-centre/news/WCMS_633284/lang–en/index.htm
  5. OECD Gender Institutions and Development Database (GID-DB).(2019), oecd.stat.org
  6. Zewude, B., Melese, B., & Habtegiorgis, T. (2021) ”The Attitude of Married Men towards Gender Division of Labor and their Experiences in Sharing Household Tasks with their Marital Spouses in Southern Ethiopia. East African Journal of Social Sciences and Humanities, 6(2), 101 – 114.
Tags:
Leave A Comment

Skip to content